ትምህርት ሚኒስቴርን በሶስት የተለያዩ ሚኒስቴር መ/ቤቶች ይከፍላል

Source: Ethiopian Broadcasting Corporation
አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ:

- ትምህርት ሚኒስቴርን በሶስት የተለያዩ ሚኒስቴር መ/ቤቶች ይከፍላል።

1. የከፍተኛ ትምህርት ስልጠና ሚኒስቴር
2. አጠቃላይ የትምህርትና ስልጠና ሚኒስቴር እና
3. የክህሎትና ስራ ፈጠራ ሚኒስቴር
- ከ1-6ኛ ክፍል ሁሉም ተማሪ በአፍ መፍቻዉ ቋንቋ ትምህርት እንዲሰጠዉ ይደረጋል።
-  ከ7-12ኛ ክፍል ለሁሉም ተማሪ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ይሰጣል።

- ከ1-12ኛ ክፍል ድረስ እንግሊዘኛ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት አይነት ይሰጣል።
-  ከ1-12ኛ ክፍል አማረኛ እና ሌላ አንድ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት አይነት ይሰጣል።

- (ለምሳሌ ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ አፋን ኦሮሞ እና አማረኛ ከ1-12ኛ ክፍል እንደ ትምህርት አይነት ይሰጣሉ ማለት ነዉ)

- 10ኛ ክፍል ላይ እየተሰጠ ያለዉ የመልቀቂያ ፈተና ይቀራል።
- አጠቃላይ ፈተና 6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ላይ ይሰጣል።
- የተማሪዎች የዩኒሸርሲቲ ቆይታ ዝቅተኛዉ 4 አመት ይሆናል።

- ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች በመጀመሪያ አመት የት/ት መርሃ ግብር እንደ ጂኦግራፊ፣ አንትሮፖሎጂ፣ ሶስዮሎጂ፣ ስነምግባር የመሳሰሉ የማህበረሰብ ሳይንስ ኮርሶችን እንዲወስዱ እና ስለ ማህበረሰባቸዉ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ይደረጋል።

- የመጨረሻ አመት ተማሪ ሲሆኑም ከ4 እስከ 8ወር ለሚሆን ጊዜ ወደ ሌላ አከባቢ በመሄድ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል።
- የመምህራን ጥቅማጥቅም በተገቢዉ መልኩ ይጠበቃል።
- ፍኖተ ካርታዉ ለ12 አመት ያገለግላል።