American Hero, Senator, Presidential contender #RiP John McCain Sad day for America🙏🇱🇷

American hero, Senator, Presidential contender, War Hero, Senator, Presidential Contender, Maverick Republican...!

John McCain died at age 81.   

Rest in Peace, Sir.
#RiP John McCain Sad day for America🙏🇱🇷

ታማኝ በየነን ለመቀበል በ አዲስ አበባ የተቋቋመው ኮሚቴ

ጀግናውን እና አቋመ ጠንካራውን ታማኝ በየነን ለመቀበል በ አዲስ አበባ የተቋቋመው ኮሚቴ ነሀሴ 18 ቀን 2010 ዓ.ም በ 9 ሰአት በ ጌትፋም ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል::
ግባ በለው ታማኝን ግባ በለው !!!!

Source: Clear Photo Studio On Facebook 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ የተመራ የልዑካን ቡድንን ጋር እየተወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ የተመራ የልዑካን ቡድንን ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ የተመራ የልዑካን ቡድን ጋር እየተወያዩ ነው። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ የተመራ የልዑካን ቡድንን በፅህፈት ቤታቸው ነው ተቀብለው እያነጋገሩ ያሉት።

በውይይታቸውም የኢትዮጵያና አሜሪካ ግንኙነትን አንድ ምዕራፍ ከፍ የሚደርጉ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን እንደሚፈፅሙ እንደሚጠበቅ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል።Source: Fana Broadcasting / #FBC

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት አለን” - ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ

“በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት አለን” - ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት አለን” ሲሉ ኮንግረስማን ክሪስ ስሚ ዝገለጹ።

በአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ የተመራ የልዑካን ቡድን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ  በጽህፈት ቤታቸው  ባነጋገሩበት ወቅት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት ያላቸው መሆኑን ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ ተናገረዋል፡፡

አሁን  ላይ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጠልም ኮንግረንስማን ክሪስ ስሚዝ መጠያቃቸውን ነው የውጭ ጉዳይ መረጃ ያመለከተው።

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት መሆኑን  የገለጹት  የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ  አሜሪካ ለኢትዮጵያ ዕድገት ለምታደርገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ኮንግረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀውም እስከአሁን ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ  በልማት፣ በዴሞክራሲ፣ በመልካም አስተዳደርና በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር መስራቷን እንደምትቀጠልም አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያና አሜሪካ አሸባሪነትን በመዋጋት እና በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ እረገድ አሜሪካ ጠንካራ አጋር መሆኗን በመጥቀስ፣ ይኸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ በጋራ ትሰራለች ሲሉም አስረድተዋል፡፡


ህግ የማስከበርና የማስፈፀም አቅሜ ፍትሃዊነት የጎደለውና ሰፊ ክፍተት ያለበት ነው – የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

ህግ የማስከበርና የማስፈፀም አቅሙ ፍትሃዊነት የጎደለውና ሰፊ ክፍተት ያለበት መሆኑን በጥናት ማረጋገጡን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ በተቋሙ የ2010 እቅድ አፈፃፀምና የ2011 እቅድ ውይይት ላይ እንደገለጹት እነዚህን ችግሮች ከመሰረቱ ለመቀየር መንግስት የተለያዩ መሻሻዎችን እያደረገ ነው።

በዚህም መንግስት በፍትህ ስርዓቱ ላይ መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ አየተወሰደ ሲሆን፥ በርካታ ዜጎች የይቅርታ ተጠቃሚ መሆን፣ የትጥቅ ትግል ማቋረጥ፣ የምህረት አሰጣጥ ስነ ስርዓት አዋጅ ማውጣት ከመሻሻያዎች ውስጥ በምሳሌነት ጠቅሰዋል።

ይሁን እንጅ ከህዝብ አመኔታና እርካታ አንፃር የፍትህ ስርዓቱ ዝቅተኛ አፈፃፀም ደረጃ ላይ መሆኑን ነው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ የገለጹት።

በዚህም ህዝብ በተደገጋሚ የሚማረርበትና የህግ የበላይነት ትርጉም ያጣበት የዴሞክራሲ ስራዓት ግንባታ ሂደቱን ገጽታ ያበላሹ ተግባራት በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሲፈጸሙ መቆየታቸውን ነው የገለጹት።

የፍትህ ስርዓቱ ነፃና ገለልተኛ በመሆን የህዝብን የህግና የፍትህ ጉዳዮችን ፍላጎትና ጥያቄዎች በሚመለልስ ደረጃ ያለመሆኑም ነው የተገለጸው።

የህግ አስከባሪ ተቋማትም ለፍትህ ታማኝ፣ ለዜጎች መብት ተቆርቋሪ እንዲሆኑ የህዝብ ፍላጎት ቢሆንም የፍትህ ተቋማቱ ይህን ፍላጎት በሚያሳካ ቁመና ላይ ያለመሆናቸውንም አስረድተዋል።

በዚህም በዜጎች ዴሞከራሲያዊና ሰባዊ መብቶች አያያዝ ላይ ክፍተቶች የተፈጠሩ በመሆኑ ሀገሪቱን ላለመርጋጋት ዳርጎጓት የነበረ መሆኑም ነው የተገለጸው።

እነዚህን ሁኔታዎች ለመቀየር መንግስት ጥናት አካሂዶ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ዘርፎች የተለዩ ዚሆን ከዚህም መካከል አንዱ የፍትህ ዘርፍ መሆኑን ነው አቶ ብረሃኑ የተናገሩት።

የ2011 የተቋሙ እቅድም በሃገሪቱ አየታየ ያለውን ለውጥ ቀጣይነት ለማረጋገጥና የህግና የፍትህ ስርዓቱን በማሻሻል የፍትህ ስርዓቱ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ የዜጎቹን ሰባዊና ዴሞክራሲያዊ መብት የሚያስከብርና እንዲሆን ለማድረግ በሚያስችልመልኩ መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎቸ አሁን የተገኘውን ነፃነት አግባብነት በጎደለው የሚጠቀሙ አካላት መኖራቸው የተመላከተ ሲሆን፥ መንግስት የዜጎችን ህይወት የመጠበቅና የህግ የበላይነትን የማስከበር ሃላፊነትቱን ለመወጣት እንደሚሰራም አስረድተዋል።

የህግ የበላይነትን በማስከበር ሂደት ሌሎች ባለ ድርሻ አካላትና ህዝብ በየደረጃው እንዲሳተፍም ጥሪ ተላልፏል።
ውይይቱ እስከሚቀጥለው ቅዳሜ የሚቀጥል መሆኑም ነው የተመላከተውSource: Fana Broadcasting