በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት አለን” - ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ

“በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት አለን” - ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት አለን” ሲሉ ኮንግረስማን ክሪስ ስሚ ዝገለጹ።

በአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ የተመራ የልዑካን ቡድን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ  በጽህፈት ቤታቸው  ባነጋገሩበት ወቅት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ አድናቆት ያላቸው መሆኑን ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ ተናገረዋል፡፡

አሁን  ላይ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጠልም ኮንግረንስማን ክሪስ ስሚዝ መጠያቃቸውን ነው የውጭ ጉዳይ መረጃ ያመለከተው።

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት መሆኑን  የገለጹት  የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ  አሜሪካ ለኢትዮጵያ ዕድገት ለምታደርገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ኮንግረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀውም እስከአሁን ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያ  በልማት፣ በዴሞክራሲ፣ በመልካም አስተዳደርና በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር መስራቷን እንደምትቀጠልም አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያና አሜሪካ አሸባሪነትን በመዋጋት እና በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ እረገድ አሜሪካ ጠንካራ አጋር መሆኗን በመጥቀስ፣ ይኸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ በጋራ ትሰራለች ሲሉም አስረድተዋል፡፡